About us

Customer service is not a
department, it
msg632561349-9197

እንኳን ወደ  መኪና ጫረታ በደህና መጡ

በሀገራችን ልዮ በሆነ መልኩ ለክቡራን ደንበኞቻችን አመቺ እና ቀላል የሆነ የ ኦንላይን መኪና ግብይት መድረክ በማዘጋጀታችን ታላቅ ኩራት ይሰማናል። 

ዛሬ ድረ-ገጻችንን ለመጎብኘት ጊዜ ስለወሰዱ እናመሰግናለን። ግባችን እርሶ አዲስ እና ያገለገሉ መኪኖችን ባሉበት ሆነው ያለምንም ውጣ ውረድ የኦንላይን ጉብኝት፣ ስለ መኪናው ሙሉ መረጃ እና ተመሳሳይ መኪኖችን ባሉበት ሆነው ዋጋ ማወዳደር እንዲችሉ  እና የግዢ አማራጮችን መስጠት ነው፣ እንዲሁም በምቾት የዋጋ ጥቅስ እንዲያገኙ ማስቻል ነው።

የሚፈልጉትን መኪና የማግኘት ፍለጋ በከፍተኛ ተስፋዎች የተሞላ ነው. ነገር ግን ለከፍተኛ ድካም እና እንግልት መጋለጦ ምንም ጥርጥር የለውም። እርስዎ ከሚያስቡዋቸው ተሸከርካሪዎች አይነት እና የዋጋ አማራጭ በተለምዶ ከሚያገኙት ደላላ ጋር ሚቀርብሎት አማራጭ በጣም ውስን ሲሆን እነሱ በሚወስኑት ዋጋ ተመን ለመገበያየት ጭምር ይገደዳሉ፣ ነገር ግን በመኪና ጫረታ ላይ፣ እርስዎ ለሚገዙት መኪና ፍላጎቶን ያማከለ ብዙ አማራጮች ሊኖሩዎት ይገባል ብለን እናምናለን።

 — ዳዊት ለገሰ, የ መኪና ጫረታ መስራች

ዋና እሴቶች



ለአኗኗርዎ ተስማሚ የሆነውን ተሽከርካሪ በመምረጥ ረገድ በእውቀት የተደገፈ ውሳኔ ለማድረግ የሚያስፈልግዎትን መረጃ ለማቅረብ በማሰብ ጥልቅ የሆነ ጥናቶችን በየለቱ እናከናውናለን።

  • ከጭንቀት ነፃ የሆነ ፋይናንስ ማመቻቸት.
  • ታዋቂ ተሽከርካሪዎች በብዙ ምርጫ ማቅረብ.
  • ከ 20 በላይ የሚሆኑ የመኪና ብራንዶች በድረገፃችን ላይ ያገኛሉ.
  • ባቅራብያዋ ስለሚገኝ ጥገና ጣብያ መረጃ ያገኛሉ
  • እንዲሁም የተለያዩ የመኪና እስፔር ፓርት ግዢ እና ማማከር አገልግሎት አቅርበናል.

የሚዲያ ጋለሪ

እኛን ሲመርጡ ሚያገኙት ጥቅሞች

መኪና መሸጥ ይፈልጋሉ?

መኪናዎ ምን ያህል ዋጋ እንዳለው ያውቃሉ? ለሽያጭ ሚያቀርቡት ተሽከርካሪዎች ፍጹም ምርጥ ሚባል ዋጋ ይቀበሉ። ሁሉንም የወረቀት ስራዎች እኛ እንጨርስሎታለን. ቀጠሮዎን ዛሬ ያስይዙ!

አዲስ መኪና እየፈለጉ ነው?

በኛ በኩል ሚገዣቸው መኪኖቻ ሁሉንም መስፈርቶች በማሟላት እና ግልፅነት የተላበሰ ግብይት እንዲሆን ደህንነቱን እናስከብራለን። በተጨማሪም መኪናዎን የትም ቦታ እናደርሳለን።

እንዴት በኦንላይን የጥገና አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ አስበዋል?

ድርጅታችን በመላው የሀገሪቱ ዋና ከተሞች ላይ ከሚገኙ ታዋቂ የጥገና አቅራቢ ድርጅቶች ጋር ጥልቅ የሆነ ግንኙነት ስላለው እርሶ እኛን በኦንላይን የጥገና ማማከር አገልግሎታችንን በመጠቀም ባቅራብያዎ ወደሚገኝ ጥገና ጣብያ ልንመራዎት እና ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኙ ቀድሞ ቦታ የማስያዝ ስራውን እንሰራሎታለን። 

ደንበኞች ስለኛ ምን ይላሉ